ሶማሊያ የገባው የኢትዮጵያ ጦር ከአልሸባብ ጋር የሚያደርገው ጦርነት እንደቀጠለ ነው

 

ታህሳስ 24 ቀን 2004 ዓ/ ም

ኢሳት ዜና:-ባለፈው ቅዳሜ በለደወይን የምትባለውን የሶማሊያን  ግዛት ከአልሸባብ እጅ መልሶ የነጠቀው የኢትዮጵያ ጦር በሚቀጥሉት ቀናት ከአልሸባብ ተዋጊዎች ብርቱ ፍልሚያ ይጠብቀዋል ሲሉ የመገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ነው።

ወል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው አልሸባብ በበለደወይን አጎራባች ስፍራዎች  ላይ የነበሩትን ተጠባባቂ ወታደሮቹን ወደ ከተማዋ በማስጠጋት ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋጋት ዝግጅት እያደረገ ነው።

በሌለ በኩል የኬንያ ጦር የአልሸባብን የኢኮኖሚ ምንጭ የሆነችውን የኪስማዩ ከተማን ለመያዝ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተመልክቷል።

የብሩንዲ እና የኡጋንዳ ሰላም አስጠባቂ ሀይላት ሞቃዲሾን ከአልሸባብ እጅ ማስለቀቃቸውን እየተናገሩ ነው።

ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት አራቱ የጎረቤት አገሮች አልሸባብን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ ጦራቸውን ቢያንቀሳቅሱም እስካሁን ድረስ አልተሳካላቸውም።

በ2006 የአለሸባብ ወታደሮች በኢትዮጵያ ጦር ላይ በፈጸሙት ጥቃት፣ ጦሩ ያለምንም ውጤት ሶማሊያን ለቆ እንዲወጣ መደረጉ ይታወሳል።