ከ900 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩት የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመታደግ ከ 10 ዓመት በፊት የተሰራው የጸሀይ እና የንፋስ መከላከያ ጣሪያ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እያመዘነ መምጣቱን የደብሩ መነኮሳት እና የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ
( ኢሳት ዜና መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ/ም ) ነዋሪዎቹ ባካሄዱት ትዕይንተ ህዝብ ላይ የደብሩ አስተዳዳሪዎች እንዳሉት ለ 5 ዓመት ተብሎ የተሰራው ከፍተኛ ክብደት ያለው ጊዚያዊ ጣሪያ ከጥቅሙ ይልቅ ሊያመጣ የሚችለው ጥፋት ሃሳብ ላይ ጥሏቸዋል
የቅዱስ ላሊበላ ገዳም መነኮሳትም ሆኑ የላስታ ህዝብ በዓለም ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ የባህል የቅርስ ተቋም የተመዘገቡት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የተጋረጠባቸውን ስጋት በተመለከተ ለሚመለከተው አካል ከ 20 ጊዜ በላይ አቤቱታ ሲያቀርቡ ኖረዋል፡፡