በቴፒ የሚታየው ችግር እየተባባሰ መምጣቱንና ግጭት ሊነሳ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን ነዋሪዎች ተናገሩ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ/ም ) ካለፉት 3 ሳምንታት ጀምሮ በከተማውና አካባቢው የተጀመረውን ተቃውሞ ተከትሎ እስካሁን 5 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ በተለይ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል አካባቢውን ከጎበኙ በሁዋላ፣ የአፈጉበኤዋን ውሳኔ ተግባራዊ ላለማድረግ ግጭቶችን እየቀሰቀሱ ነው።
በቴፒ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ለ3 ዓመታት ታስሮ በቅርቡ በምህረት የተለቀቀው አቶ ሚስጢሩ ሲሳይ እንደተናገረው፣ የለውጡ እንቅስቃሴ ቴፒ አልደረሰም ብሎአል። ችግሩ ካለፉት 27 አመታት ጀምሮ የሚታይ ቢሆንም፣ በህወሃት ገንዘብ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች አሁንም በአካባቢው ችግር እያደረሱ ነው።
ሸካ ዞን ላይ የአንድ ብሄረሰብ አባላት ሙሉ በሙሉ ስልጣኑን መቆጣጠራቸውንና የአማራ ተወላጆችን ከአካባቢያቸው ለማስወጣት ሙከራ ማድረጋቸውን ተናግሯል።
አቶ ሚስጥሩ ጥያቄያቸው የእኩልነትና የመልካም አስተዳደር መሆኑን ይናገራል። በዞኑ በሁሉም መስሪያ ቤቶች የአንድ ብሄረሰብ ተወላጆች ተቆጣጥረውት እንደሚገኙ ገልጿል።