ፍርድ ቤት አቶ አብዲ ኢሌና ግብረአበሮቻቸው ያቀረበትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገው
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) የቀድመው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ እና ሌሎች 3 ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን የዋስትና መብት ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረግ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። 19ኛው የወንጀል ችሎት የተከሳሾችን የዋስትና ጥያቄ ለማየት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጅ የተከሰሱበት ወንጀል የዋስትና መብት የማያሰጥ መሆኑን የጠቀሰው ፍርድ ቤቱ፣ አቶ አብዲ በእስር ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉና ለመስከረም 4 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በሌላ በኩል የክልሉ ፖለስ አዛዥ የነበሩት ፈርሃን ተሃሪ ተይዘው ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ኮሚሽነሩ ሄጎ የሚል የወጣቶች ቡድን በማዘጋጀት በክልሉ ረብሻ እንዲነሳ በማድረግ ለሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆነዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።