የራያ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ሰፋሪዎች መምጣታቸውን ተቃወሙ

የራያ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ሰፋሪዎች መምጣታቸውን ተቃወሙ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በትግራይ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ትዕዛዝ 600 የሚሆኑ በአድዋና አዲግራት አካባቢ የነበሩ ሰዎችን በአላመጣና አካባቢው እንዲሰፍሩ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ተገቢ አይደለም።
የአካባቢው ተወላጆች እንደሚሉት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች መሬት አልባ ሆነው እንዲሁም የመሬት ጥያቄ አቅርበው መልስ ባላገኙበት ሁኔታ አርሶአደሮችን አምጥቶ ማስፈር በአካባቢው ግጭት እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው። ይህንኑ ተከትሎ የአካባቢው ተወላጆች ተቃውሞ ለማሳመት ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ተወላጆቹ ተናግረዋል። ቤታቸው ፈርሶባቸው በየቦታው ወድቀው የሚገኙ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ባለበት ጊዜ ሰዎቹን ከተለያዩ አካባቢዎች አምጥቶ ማስፈሩም ትክክል አለመሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።