ኢትዮጵያና ሱዳን በጋራ ድንበራቸው ላይ ከሁለቱ አገራት የተውጣጣ ጥምር ጦር ለማሰማራት መስማማታቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 11 ቀን 2010 ዓ/ም ) ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር በገበሬዎች መካከል ግጭቶች ሲከሰቱ መቆየታቸው ይታወሳል።
አሁን በድንበሮቻቸው ላይ ከሁለቱም ሀገራት የተውጣጣ ጦር ለማሰማራ የወሰኑት ፣ የሁለቱአገራት ጦር ኢታማዦር ሹሞች ትላንትናው ካርቱም ላይ ተገናኝተው ከመከሩ በኃላ ነው።
በድንበር አካባቢ የሚሰፍረው የሁለቱ አገራት የጋራጥምር ጦር ሽብርተኝነትን፣ ድንበር ዘለልየአማፂያን እንቅስቃሴን እና ህገ ወጥ ስደትንየመከላከል ተልዕኮ እንደተሰጠው፣የሱዳን መከላከያ ኃይል አዛዥ ከማል አብዱል ማዕሩፍ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክተዋል።
ከኢትዮጵያ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት ጠቅላይኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን በበኩላቸውበሀገራቱ ድንበር ላይ የሚሰፍረው ጥምር ጦርየቀጠናውን ሰላምና መረጋጋት በማረጋገጥ በኩል ጉልህ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።