አዲሱ የአዲስ አበባ ከንቲባ ካቢኔያቸውን ሊያዋቅሩ ነው
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 03 ቀን 2010 ዓ/ም ) ነሃሴ 4 ቀን 2010 ዓም አዲሱ የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ አዲስ ካቢኔ ሊዋቅሩ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። 17 በሚሆኑ የቢሮ ሃላፊነት ቦታዎች የካቢኔ አባላት በቀጥታ እንደሚሾሙ ሲጠበቅ፣ ከተማዋን እንደፈለጉ ሲመሩ የነበሩት የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተወልደ ወ/ጻዲቅ በደቡብ ክልል የድርጅት ሃላፊው በአቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከስልጣን እንደሚነሱ የተነገራቸው ባለስልጣናት በከፍተኛ ሀዘን ተውጠው መታየታቸውን ምንጮች አክለው ተናግረዋል። የካቢኔ አባላቱ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2011 ዓም እንደማይለወጡ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ ውሳኔው በአፋጣኝ ተቀይሮ አዲስ ሹም ሽር ይካሄዳል።
አዲሱ ከንቲባ ቀድሞ የነበሩትን የቅጥር ግቢው የጥበቃ ኃላፊዎች ሙሉ ለሙሉ ቀይረው በአዲስ የተኳቸው ሲሆን ፣ ይጠቀሙበት የነበረውን ተሽከርካሪ ሳይቀር በቶሎ እንዲያስረክቡ አድርገዋቸዋል።