(ኢሳት ሐምሌ 26/2010)የአብዲ ኢሌን አገዛዝ የሚቃወሙ የክልሉ ተወላጆች ሁለተኛ ስብሰባዎችን በድሬዳዋ ከተማ ላይ በማካሄድ ላይ ናቸው። የክልሉ የአገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል። ባለፈው አዲስ አበባ ላይ ተደርጎ የነበረው የመጀመሪያው ስብሰባ በአብዲ ኢሌ ደጋፊዎች የተደናቀፈ ቢሆንም፣ ዛሬ የተጀመረው የድሬዳዋው ስብሰባ ግን እስካሁን በሰላም እየተካሄደ ነው። የስብሰባው አስተባባሪዎች እንደሚሉት፣ ሶስተኛውን ስብሰባ ጅግጀጋ ላይ ለማድረግ እቅድ አላቸው።
አስተባባሪዎቹ ከዚህ በሁዋላ ምንም የሚፈሩት ነገር እንደሌለና አብዲ ኢሌ ስልጣን እስኪለቅ ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።