አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደኢሕዴን ሊቀመንበርነታቸው ለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010) አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደኢሕዴን ሊቀመንበርነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ።

የደኢሕዴን ሊቀመንበር ከሆኑ ሶስት ወር ያልሞላቸው አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የለቀቁበት ምክንያት ግን አልታወቀም።
በቅርቡ በሃዋሳ በተፈጠረው ግጭት የሲዳማ ዞን እና የወረዳ አመራሮች በፈቃዳቸው ስልጣን እንዲለቁ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ከግጭቱ ጋር በተያያዘ 226 ሰዎች መታሰራችውም ታውቋል።
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለኢሕአዴግ ሊቀመንበርነት ከዶክተር አብይ አህመድ ጋር መወዳደራቸውም ይታወሳል ።
አቶ ሽፈራው በአሁኑ ወቅት የግብርና ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ ሲሆን፣ይህንን ስልጣናቸውን ስለመልቀቃቸው የታወቀ ነገር የለም።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ሙፍሪያት ከማል የደኢሕዴን ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ታውቋል።