በይርጋጨፌ ትናንት በነበረው ግጭት ቤቶች ተቃጠሉ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ/ም) በጉጂና በጌዲዮ ብሄረሰቦች መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ አንዳንድ የደኢህአዴን አመራሮች ያሰማሯቸው የአካባቢው ባለስልጣናት “እኛ ተረጋግተን ሳንኖር እናንተ በእኛ ቦታ መኖር አትችሉም” በሚል የአካባቢውን ወወጣቶች አደራጅተው በጉራጌ፣ በአማራና በሌሎች ብሄረሰቦች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ማድረጋቸውን የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል። ትናንት ምሽት የተለያዩ ሰዎች ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን ዛሬ፣ ብዙዎቹ የንግድ ድርጅቶቻቸውን ዘግተው ውለዋል። ተጨማሪ ጥቃት ይፈጸማል በሚል የከተማ ነዋሪዎች በስጋት እያሳለፉ መሆኑን ተናግረዋል። በአካባቢው ወታደሮች የሌሉ በመሆናቸው ስጋታቸውን እንዳባባሰው ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል።