በአማሮ ወረዳ ትናትን በነበረው ግጭት የሰዎች ህይወት አለፈ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ/ም) ከድንበር ማካከለል ጋር በተያያዘ በጉጂና በኮሬ ማህበረሰቦች መከካል የተጀመረውና ለአንድ አመት የዘለቀው ግጭት ደም አፋሳሽ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን፣ ከአማሮ በኩል ከዶርባዴ ቀበሌ ልዩ ስሙ በርበሬ ከሚባል አካባቢ አንድ አርሶአደር ሲቆስል፣ ምንም እርምጃ አልወሰዱም በሚል ህዝቡ ተቃዉሞ ያስነሳባቸው ሁለት የመከላከያ አባላትም ሲጎዱ፣ አንደኛው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በህክምና ላይ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ወታደሮች ሶስት የጉጂ ኦሮሞ ማህበረሰቦችን ሲገድሉ ሰባት ደግሞ አቁስለዋል።
በጉጂ በኩል የሞቱትን ለማወቅ ባይቻልም፣ ግጭቱ ከተጀመረበት ከሃምሌ 2010 ዓም ጀምሮ በኮሬ በኩል 52 ሰዎች ተገድለው ከ100 በላይ ቆስለዋል። ከቡሌ ሆራና ከወረዳዉ ቆላማ ቀበሊያት/በተለይ ከዶርባዴና ጀሎ/ የተፈናቀሉ ከ 20፣ ሺ በላይ ዜጎችም እገዛ በማጣት ለከፋ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
ከአማሮ ዲላ የሚወስድ መንገድ ዛሬም ዝግ እንደሆነ ነው።