በሶማሊ የአገር ሽማግሌዎች ላይ የሚደርሰው ወከባ ጨምሯል

በሶማሊ የአገር ሽማግሌዎች ላይ የሚደርሰው ወከባ ጨምሯል
(ኢሳት ዜና ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ/ም) የህወሃት ታጣቂዎች የአብዲ አሌን አገዛዝ በመቃወም ለፌደራል መንግስቱ አቤቱታ ለማሰማት በተንቀሳቀሱ የአገር ሽማግሌዎች ላይ አሁንም ዛቻና ማስፈራሪያ እያሰሙ ነው። ዛሬ 10 አሮ አብዲ አሌን የሚቃሙ የክልሉ ተወላጆች በታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የአነጋገርናቸው የክልሉ ተዋላጆች ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ሼክ አብዲ ዱብ እና ሼክ አብዲ ቡሉህ የተባሉ የሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ኦሮሞዎች ከሶማሊ ክልል ሲፈናቀሉ በመቃወማቸው ብቻ ከአንድ አመት በላይ በእስር ሲሰቃዩ ከቆዩ በሁዋላ፣በጅግጅጋ ከተማ በተሰየመው ፍርድ ቤት እያንዳንዳቸው በ5 አመት ጽኑ እስራት ተቀጠዋል።
የሶማሊ ክልል ህዝብ በአቶ አብዲ አሌ ላይ የጀመረው ተቃውሞ እንደቀጠለ ሲሆን የዶ/ር አብይ አህመድ መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን አስተያየት አልሰጠም።