(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 30/2010) ሜጀር ጄነራል አለምሸት ደግፌ እና ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ማዕረጋቸው ተመለሰ ።
የሁለቱ ከፍተኛ መኮንኖች ማዕረግ የተመለሰው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ውሳኔ ነው።
ሜጀር ጄነራል አለምሸት ደግፌ እና ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ በምርጫ 1997 ማግስት ሕዝባዊ አቋም በመያዛቸው ማዕረጋቸውን ተገፈው በተራ ወታደርነት ከሰራዊቱ የተባረሩት በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ትዕዛዝ ነበር።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው ሁለቱ ጄነራሎች ለሃገራቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ማዕረጋቸውን ከመመለስ ባሻገር የጡረታ መብታቸው እንዲከበርም ተወስኗል።