አይ ኤም ኤፍ ኢትዮጵያን የእዳ ጫና ከበዛባቸው አገራት ተርታ መደባት
(ኢሳት ዜና ግንቦት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) የአላማቀፉ የገንዘብ ድርጅት እንደሚለው ለአመታት መካከለኛ የእዳ ጫና ካለባቸው አገራት ስትመደብ የቆየችው ኢትዮጵያ ፣በዚህ አመት ከፍተኛ የውጭ እዳ ካለባቸው አገራት መካከል ተመድባለች::
እንደ ኢትዮጵያ አደጋ ውስጥ የገባችው ሌላዋ አገር ዛምቢያ ናት:: ኢትዮጵያ በተለይ ከግል ባንኮች የምትበደረው ገንዘብ እየጨመረ መምጣት አሳሳቢ መሆኑን ድርጅቱ ጠቅሷል::
የውጭ እዳን ወለድ ለመክፈል የሚወጣው ወጭ እየናረ መምጣቱን የጠቀሰው የገንዘብ ተቋሙ ቢሆንም አገሮች አሁንም ለመሰረተ ልማት ግንባታ በሚል ተጨማሪ ገንዘብ ለመበደር ማሰባቸውን ጠቅሷል::
ኢትዮጵያ ከ 40 ቢሊዮን ዶላር ያላነሰ እዳ አለባት ::