የሱዳኑ ፕሬዝዳትን አልበሽር የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አዘዙ

 

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 3/2010) የሱዳኑ ፕሬዝዳትን ኦማር ሃሰን አልበሽር በሃገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ትዕዛዝ አስተላለፉ።

ትዕዛዙ የተላለፈው በሃገሪቱ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሌሎች ቡድኖች በብሔራዊ ደረጃ በሚካሄደው ውይይት ላይ ለመሳተፍ በቅድሚያ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በጠየቁት መሰረት መሆኑ ታውቋል።

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር  ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች ለመልቀቅ ከውሳኔ ላይ የደረሱት በተቃዋሚዎች ጫና ነው ይላል ሮይተርስ በዘገባው።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1998 በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከያዙ ጊዜ አንስቶ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ለድርድር መንገዱን ዝግ አድርገው ቆይተዋል።

በአሁኑ ሰአት ግን ኦማር አልበሽር በ2020 የሚካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታት የፖለቲካ ምህዳሩን ለድርድር ክፍት ማድረጋቸውን ነው ለማወቅ የተቻለው።

ከ2015 ጀምሮ በተደጋጋሚ ውይይቶች ላይ የቆዩት ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ለሀገሪቱ ቀጣይ እጣ ፈንታ ትልቅ ሚና የኖረዋል ብሏል ዘገባው።

ባለፈው ወር 80 እስረኞች የተፈቱ ሲሆን በተቃዋሚዎች ጎራ ግን ገና 50 ይቀራሉ መባሉን ዘገባው አመልክቷል።