በጎንደር የባጃጅ አሽከርካሪዎች አድማ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) አሽከርካሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣ ትናንት ጠዋት የወታደራዊ እዙ አመራሮች ናቸው የተባሉና የከተማው ጸጥታ ሃላፊ ዘለቀ የሚባል ሰው በሲኒማ አዳራሽ በጠሩት ስብሰባ የባጃጅ አሽከርካሪዎች አድማ እንዳያደርጉ አስጠንቅቀዋቸዋል። አሽከርካሪዎች የዋጋ ተመን ቅናሽ እንዲያደርጉ፣ አርማ የሌለበትን ሰንደቅ አላማ እንዳያደርጉ፣ የኢትዮጵያ ካርታ፣ ኢትዮጵያ አገሬ የሚል ጽሁፍ እንዲያነሱ፣ የነጋስታቱን ፎቶ እንዲያወርዱ ካላወረዱ ግን ኮማንድ ፖስቱ እርምጃ እንደሚወስድባቸው ተነግሯቸዋል። ሾፌሮቹ ይህን በመቃወም ስብሰባ አቋርጠው ከወጡ በሁዋላ፣ እንደገና አስገብተው ትዕዛዙን ነግረዋቸዋል።
በጎንደር ከተማ ከፍተኛ የውሃ፣ የመብራትና የነዳጅ እጥረት ያለ በመሆኑ ህዝቡ ለከፍተኛ ስቃይ ተዳርጓል።