በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ በተካሄደው ተቃውሞ የአንድ ሰው ህይወት ጠፋ
(ኢሳት ዜና የካቲት 8 ቀን 2010ዓ/ም) ትናንት በስራ ማቆም አድማ የተጀመረው የወልቂጤ ተቃውሞ ዛሬ ወደ አደባባይ ተቃውሞ ተለውጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ውለዋል። “ በኢህአዴግ መገዛት በቃን፣ የታሰሩት ይፈቱ፣ ለውጥ እንፈልጋለን” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች አሰምተዋል። በተቃውሞው አንድ ሰው ሲገደል ሌሎች 3 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። 7 መኪኖች ተቃጥለዋል። የዞን ፋይናንስ ጽ/ቤትና የዞን ድርጅት ጽ/ቤት ሰነዶች ተቃጥለዋል። አንድ የደህንነት ሰራተኛን የቤት እቃዎችንም ማውደማቸውን ወጣቶች ተናግረዋል። አቶ ታሪኩ የሚባል የመሬት አስተዳዳር ሃላፊም በከፍተኛ ሁኔታ ተደብድቧል።