ጥቅምት ፳፩ (ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃረር ዙሪያ ወረዳዎች የሚገኙ አርሶአደሮች ሜንጫ የተባለውን ባህላዊ መሳሪያቸውን ይዘው ወደ ከተማ እና እርሻ ቦታቸው ሲሄዱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማንኛውም የጦር መሳሪያ መያዝ ይከለክላል በሚል መሳሪያቸውን ተቀምተው የተሰወሰኑት ደግሞ መታሰራቸው ታውቋል።
ሜንጫ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ለእርሻ ስራ እና ሌሎችም አገልግሎቶች ስራ ላይ የሚውል ሲሆን፣ የአካባቢው አርሶአደሮች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ይዘውት ይዞራሉ።