በአዘዞ የሚገኙ ወታደሮች ግድያውን በእነሱ ስም የሚፈጽሙት የህወሃት ልዩ ሃይል አባላት ናቸው አሉ

ነሃሴ  ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወታደሮቹ እንደሚሉት የኦሮሞ፣ አማራ እንዲሁም የደቡብ ክልል ወታደራዊ አዛዦች በሰሜን ጎንደር በሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ አመራር መስጠት አቁመዋል።

3 ወታደራዊ አዛዦችን የገደሉ ከ70 ያላነሱ የሰራዊት አባላት አለመመለሳቸውንም የ24ኛ ው ክ/ጦር አባላት ተናግረዋል። ወታደሮች በህዝብ ላይ ምንም አይነት እርምጃ እንዳይወሰዱም ምክራቸውን ለግሰዋል

ሰሞኑን በርካታ የጦር መሳሪያዎች በወለቃ፣ እና በገነት ተራራ አካባቢዎች ወድቀው መገኘታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ወታደሮቹ ስርዓቱ ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ ካልፈለገ ፣ ከህዝብ ጋር እየተጋጨን መቆየት አንፈልግም በማለት ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ ቆይተዋል።