በአቶ አሊ መኪ ላይ የ 15 አመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት

ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አሊ በኡስታዝ አቡበክር አህመድ መዝገብ ተከሶ የሚገኝ ሲሆን፣ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፣ በሌሉበት የ15 አመት ጽኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።
ታህሳስ 23/2005 የዋለው ችሎት አቶ አሊን በነጻ ቢያሰናብታቸውም፣ አቃቢ ህግ ይግባኝ ብሎባቸው ክሱ እንደገና እንዲታይ ተደርጓል።
በአቶ አሊ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በሌሎች የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ ሊሰጥ የታሰበውን ፍርድ አመላካች ሊሆን እንደሚችል አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።
ፍርድ ቤት የመጨረሻው ውሳኔ የመስጫ ጊዜውን በተደጋጋሚ ሲያራዝም ቆይቷል። በመንግስት የቀረበውን የሽብረተኝነት ክስ አብዛኛው ሙስሊም አይቀበለውም።