በጀርመን የኢትዮጵያ ኢምባሲ የተዘመረው መዝሙር ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጠረ

ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው የግንቦት20 በአልን ለማክበር ጀርመን በርሊን ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ ያልተጠበቀ ክስተት መታየቱን ምንጮች ገልጸዋል።
በዝግጀቱ ላይ የኢትዮጵያና የጀርመን ከፍተኛ ባለስልጣናት በእንግድነት ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር ያለምንም ችግር የተፈጸመ ቢሆንም፣ የጀርመን ብሄራዊ መዝሙር በሚዘመርበት ጊዜ ግን የጀርመንን ባለስልጣናት ያስደነገጠ መዝሙር ቀርቧል። የኢትዮጵያ ኢምባሲ የጀርመን ብራሄራዊ መዝሙር ብሎ ያቀረበው
በሂትለር ጊዜ የተዘመረ ሲሆን፣ በስፍራው ያሉትን ባለስልጣናት ካስደነገጠ በሁዋላ እንዲቋረጥ ተደርጓል።
የኢሳት ምንጮች እንደሚሉት ሃላፊነቱን ወስዶ ስራውን ሲያስተባብረው የነበረው የኢምባሲው ሰራተኛ ወደ ኢትዮጵያ በስቸኳይ እንዲመለስ ተጠርቶ ተመልሷል። ሰራተኛው ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጠብቀው በመፍራቱ ሲጨነቅ መታየቱን የደረሰን
መረጃ ያመለክታል። በጉዳዩ ዙሪያ በርሊን የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለማነጋገር ሞክረን አልተሳካልንም።