በአምቦ ተማሪዎች ታሰሩ

በምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ሊግ ለኢሳት በላከው መግለጫ ፣ አምና በሚያዚያ ወር ከ79 በላይ የኦሮሞ ወጣቶች በአምቦና አካባቢዋ ከተገደሉ በሁዋላ፣ ባለፉት 10 ቀናት ደግሞ 50 የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መያዛቸውን ገልጿል፤፡ ከ20 በላይ ወጣቶች በድብደባ ጉዳት ደርሶባቸው በአምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ።
ድርጅቱ ባሰባሰበው መረጃ በእስር ላይ የሚገኙ 20 ተማሪዎችን ስም ይፋ አድርጓል። ወጣቶቹ የታሰሩት የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች በመሆናቸው መሆኑንም የሰብአዊ መብት ሊጉ ገልጿል።