የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳን ሊሄዱ ሲሉ ተያዙ የተባሉት 101 ኢትዮጵያውያን ኬንያ ፍርድ ቤት ቀርበው 50 ሺ የኬንያ ሸልንግ መቀጣታቸውን፣ ቅጣታቸውን ካልከፈሉ ደግሞ በአንድ አመት እስር ተቀጠው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተወስኖባቸዋል።
ኢትዮጵያውያኑ በምግብ እጥረት የተነሳ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎሳቁለው ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተዘግቧል።
መንግስት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማግኘቱን በመገናኛ ብዙሃን በተደጋጋሚ ቢገልጽም አገሪቱን እየጣሉ የሚሰደዱ ዜጎች ቁጥር ሲጨምር እንጅ ሲቀንስ አለመታየቱን መረጃዎች ያሳያሉ።