ጥር ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአመዛኙ ኢትዮጵያውያን፣ ሶማሊያውያንና የአካባቢው ሀገራት ዜጎች እንደሆኑ የሚገመቱ ስደተኞች ሲጓዙባት የነበረች አነስተኛ ጀልባ ቀይ ባህር ሰጠመች።
<<ሳባ>>የተሰኘው የየመን መንግስት የዜና አገልግሎት ጀነራለ ሳሊህ አልሰብሪ የተባሉ የሀገሪቱን ባለስልጣናት ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው ስደተኞቹን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ <<ታይዚ>>ተብላ ወደምትጠራው የየመን ደቡባዊ ምእራብ ግዛት ስታመራ ነው በመጥፎ አየር ሳቢያ የሰጠመችው።
በጀልባዋ ሲጓዙ ከነበሩት 49 ስደተኞች መካከል መንግስታቸው ባደረገው ጥረት የ 13 ስዎች ህይወት መትረፉን የተናገሩት ጀነራል ሳሊህ፤ ቀሪዎቹ 35 ስደተኞች ግን መስጠማቸውንና እስካሁን የት እንደደረሱ አለመታወቁን ገልጸዋል:: ከተረፉት 13 ሰዎች መካከል 9ኙ ኢትዮጰያውያን፣ 5ቱ ደግሞ ሶማሊያውያነ መሆናቸውንም ባለስልጣኑ አመልክተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መግለጫ በቀይባህር በኩል ተሻገረው ወደ የመን ከሚሄዱ አፍሪክውያን መካከል
በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ በሺህዎች የሚቆጠሩት ሕይወታቸውን ያጣሉ።