ሃይቅ ከተማ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ በእሳት ወደመ

ጥር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ዞን በተሁለደሬ ወረዳ ሀይቅ ከተማ የሚገኘው  የሙያና ቴክኒክ ትምህርት ቤት ሰኞ ጥር 18፣ 2007 ዓም ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ መውደሙን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። ቃጠሎው የተነሳው ከምሽት 1:30 አካባቢ ሲሆን ለ2 ሰአታት ያክል መቆየቱንና  የተማሪዎችን መረጃ ላፕቶፖ ኮምፒዩተሮች፣ ዴስክ ቶፖች እና የተለያዩ የሰርቬ ጂፒኤሶችን ማውደሙ ተውቋል።  ከኮምቦልቻ ከተማ የተነሳው የእሳት አደጋ መኪና እሳቱን ለማጥፋት ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል።

የቃጠሎው መንስኤ እስካሁን አለመታወቁን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።