ኀዳር ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግሎባል ፋይንሻል ኢንተግሪቲ ባወጣው ዘገባ በዚህ ሳምንት የቡድን 20 አገራት በአውስትራሊያ በሚያደርጉት ስብሰባ በህገወጥ መንገድ ገንዘብ በሚያዘዋውሩ ኩባንያዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል።
ተቀማጭነቱ አሜሪካ የሆነው ድርጅት በዋጣው ዘገባ፣ ኩባንያዎች ሽያጮቻቸውን፣ ታክሶቻቸውን፣ ትርፋቸውና ኪሳራቻውን ግልጽ እንዲያደርጉ መመሪያ ሊወጣላቸው ይገባል ብሎአል።
ታዳጊ አገሮች በእነዚህ ኩባንያዎች የተነሳ በእየአመቱ 1 ትርሊዮን ዶላር እንደሚያጡ ድርጀቱ ገልጿል።
ታክስ ማጭበርበርና ገንዘብን በህገወጥ መንገድ ማስወጣት የአለማችን በሽታ ሆኗል ሲል ድርጅቱ በመግለጫው ጠቅሷል።
ድርጀቱ ከሁለት አመት በፊት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ በ8 አመታት ውስጥ ወደ 11 ቢሊዮን የሚጠጋ ዶላር በህገወጥ መንገድ ከአገር ወጥቷል።