ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኖርዌይ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በተጠራ ጉባኤ ላይ የተገኙትን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በመቃወም የተጠራው ሰልፍ የአገሪቱን ዋነኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢነርኬን ሽፋን አግኝቷል።
ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በተጠራው ተቃውሞ፣ ኢትዮጵያውያን የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ ኖርዌይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ከሚፈጽመው መንግስት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት እንድታቆም ጠይቀዋል።በኢትዮጵያ ለሚታየው የሰብአዊ መብት
ጥሰት ኖርዌይ ተጠያቂ መሆኗንም ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደ/ር ቴዎድሮስ ወደ ሆቴላቸው ሲያመሩ መኪናቸው በእንቁላል መደብደቡ የአገሪቱን የሚዲያ ትኩረት ስቧል።