ለዝክረ መለስ በሚል የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰራተኞች ስራቸውን አቋርጠው ውይይቱን እንዲሳተፉ ታዘዙ

ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዝክረ መለስ 2ኛ የሙት ዓመት አከባበርን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በነበረው የፓናል ውይይት

የመንግስትንስራተኛው ለግማሽ ቀን ስራ ሳይሰራ መዋሉን ዘጋያችን ገልጿል። በተለያዩ ቦታዎች የተዘጋጁትን የፓናል ውይይቶች የመስተዳድሩ የአመራር

አባልአቶፋቃዱወ/አረጋይ፣ የአዲስአበባሴቶችናወጣቶችቢሮኃላፊና የምክትል ቢሮኃላፊበተናጠልመርተዋል። የወጣቶች መድረክ በሃገር ፍቅር አዳራሽ ፣የሴቶችመድረክበአዲስአበባማዘጋጃቤትየባህልአዳራሽእንዲሁምየልዩልዩአካላትመድረክበስድስትኪሎበሚገኘው የባህልማዕከልየፓናልውይይትተካሂዷል።

በሶስቱም ውይይቶች  ለተሳታፊዎችየሃሳብናየጥያቄማቅረቢያሰዓትበተጊቢውመንገድያላተሰጠሲሆንሁሉም የመድረኩ ተናጋሪዎች  አቶ መለስዜናዊን በማወደስ

ላይ ትኩረት አድርገው ነበር። በመድረኩ ላይ አቶ መለስዜናዊአዋቂመሪ፣የሰብዓዊመብትታጋይ፤ የአፍሪካመሪ፤ የመልካምአስተዳደር ችግርን የፈታ መሪ፤

የአለምመሪ፤ አለማቀፋዊ ደረጃ ያለው ጭንቅላት ባለቤት፣ ተዝቆ የማያልክ የእውቀትምንጭእንደነበር ተወስቷል። የመለስ ሌጋሲንብቻእየመነዘሩመሄድ

እንደሚገባ የተነገረ ሲሆን መለስበመሪነትዘመኑበተለያየጊዜያደረጋቸውንቃለመጠይቆችማንበብእንደሚገባ ለሰራተኛው ተነግሯል። መለስ “ድህነትንያስወገደ

፤የሃገርናየትውልድችግርየቀረፈ፤የመልካምአስተዳደርችግርንገናተማሪእያለ ጀምሮ የሚያውቅ ፤የውጪ ጉዳይ ፖሊሲው በሰላምና በድህነት ላይ ብቻ እንዲመሰረት ያደረገ፤የኢትዮጵያንሉዓላዊነትያስከበረ፤በአፍሪካመሪዎችናበዓለምመሪዎችስብሰባላይተጽእኖሲፈጥርየነበረ፤በእውቀትናበንባብላይየተመሰረተትንታኔየሚሰጥ፣

የህዳሴግድብንመሰረትየጣለታሪካዊመሪ” መሆኑን በማወቅ ፣ ማንኛውም ዜጋ የእሱን ሌጋሲ ማስቀጠል እንዳለበት በመድረኩ ላይ ተወስቷል። የመለስሌጋሲ

የአፍሪካምሌጋሲእንደሆነም ተገልጿል። በማዘጋጃቤትበነበረው የሴቶች መድረክ  ከተሳታፊሴቶችምንምጥያቄሳይነሳውይይቱያለቀሲሆን ፣ መድረክ ላይ

ስታወያይየነበረችሁየአዲስአበባከተማሴቶችወጣቶችናህፃናትቢሮኃላፊበመድረኩላይማይክራፎኑን ተቀብላ ማልቀሷን ዘጋቢያችን ገልጻለች። በሀገርፍቅር

በነበረውመድረክደግሞ ስለመለስ ብዙ ገለጻዎች ከተሰጡ በሁዋላ፣ ተሳታፊው አስተያየት እንዲሰጥበት እድልሲቀርብ፣ አንድ ተሳታፊ ” ስለመለስብዙተብሏል ፣ ነገርግንበአዲስአበባብዙቁጥርያላቸውዜጎችዳቦመብላትአልቻሉም፤የኑሮውድነቱሰማይነክቷል፣እናንተድህነትጠፍቷልትላላችሁ..”እያለመናገር ሲጀምር፣ መድረክ

ላይ ያሉ ሰዎች አስቁመውታል።

ጠያቂው ያነሳውን ጥያቄ ለመደገፍና ንግግሩ እንዲቋረጥ መደረጉን ለመቃወም በሚመስል መልኩ አዳራሹ በጭብጫ የተናጋ ሲሆን ፣ የመድረኩ መሪዎች ”

እንዲህአይነትጥያቄዎችበሌላ የመልካምአስተዳደርመድረኮችየሚመለሱበመሆናቸውናየዛሬውውይይትበዝክረመለስላይብቻማተኮርእንደለበትበማሳሰባቸውከድጋፍ

ማብራሪያውጪሌላ የተቃውሞ ሃሳብ ሳይነሳ መቅረቱን በውይይቱ የተሳተፈው ዘጋቢያችን ገልጿል። አወያዩአቶፋቃዱወ/ገብርኤል “አንድ በሽተኛ የሬዲዮእናቴሌቪዥጣቢያአለ፣ኢትዮጵያንበመንግስታዊድርጅቶችእንድትጥለቀለቅአድርጌበእርዳታሃገሪቱንእመራታለሁብሎየሚያስብብለውየተናገሩ ሲሆን፣

የጣቢያውን ስም ከመግለጽ ተቆጥበዋል። ንግግራቸውን በመቀጠልም “መንግስትስለልማትይለፈልፋል! መብራትግንይጠፋል፤መንግስትስለልማትይለፈልፋል!

ውሃግንይጠፋል፤  መንግስትስለልማትይለፈልፋል! ትራንስፖርትግንይጠፋል” በማለት ህዝቡ እንደሚናገር ገልጸው፣  ይህአስተሳሰብእንደማይጠቅም፣ የያዝነውንልማት

በአግባቡይዘንለሌላውንጠንክረንመስራትብቻነውየሚያዋጣን ብለዋል። በ3ቱምመድረኮች  ተሳታፊየነበሩትበአዲስአበባመስተዳድርስርየሚገኙከወረዳናክ/ከተማ

በላይያሉየሁሉምቢሮዎችናተቋማትሰራተኞችናቸው፡፡ ኢሳት ዝክረ መለስ በአል አከባበር ዝርዝር መመሪያው የደረሰው ሲሆን፣ ከመመሪያው ለመረዳት እንደሚቻለው

መለስና ልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት፣ መለስና የህዳሴው ግድብ፣ መለስና የድህነት ጥላቻ፣ መለስና ብህሃነትን በብቃት ማስተናገድ፣ መለስና የረቀቀ የዲፕሎማሲ

ትግል በሚሉ ርእሶች ዙሪያ በመላው አገሪቱ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፤ ከዚህ በተጨማሪ መለስ በራሱ ንግግር በተመረጡ ጉዳዮች ላይ ያደረጋቸው ንግግሮች በሚዲያ

እንዲቀርቡ እንዲደረግ በመመሪያው ላይ ተቀምጧል። በሌላ ዜና ደግሞበአዲስአበባሚሊኒየምአዳራሽበጠ/ሚ/ርኃይለማርያምደሳለኝየሚመራ 2ኛውሃገራዊየመልካም

አስተዳደርውይይትእየተካሄደ ነው።የከፍተኛት/ትተቋማትአመራሮች፤የክልልመስተዳድሮች፣ የቢሮኃላፊዎችናሚኒስትሮችስብሰባእያካሄዱመሆኑ ታውቋል።

አቶ አዲሱ ለገሰ ኢህአዴግ በገጠመው የአመራር ችግር የተነሳ የትራንስፎርሜሸንኑን እቅድ ለማሳካት አለመቻሉን መግለጻቸው ይታወቃል።ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች

እያደረጉት በሚገኘው ስብሰባ የአመራር ችግሩ ዋናው የመመያያ አጀንዳ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።