ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዩክሬን መንግስትና በአማጽያኑ መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ሩሲያ በመቶዎች
የሚቆጠሩ ከባድ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስፍራው ማንቀሳቀሱዋ ውጥረቱን ወደ አደገኛ ጫፍ ላይ እንዳደረሰው አለማቀፍ ብዙሀን
መገናኛዎች እየዘገቡ ነው።ቢቢሲ እንዳለው፤የሩሲያ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ዩክሬን ድንበር መጠጋታቸውን ተከትሎየዩክሬን አማጽያን
የተቆጣጠሩዋትዶኔትስክ ከተማ በከባድ ፍንዳታ ተናውጣለች።ፍንዳታውን ተከትሎ የመንግስት ሰራተኞችና ነዋሪዎች ከቢሮአቸውና
ከመኖሪያቸው በመውጣት ወደ ከተማዋ ማእከላዊ ቦታ ተሰባስበው ታይተዋል።ትናንት ምሽት ላይ እርዳታ የጫኑ ከመቶ በላይ የሩሲያ
ከባድ ተሽከርካሪዎች የሉሀስንክን ክልል አቁዋርጠው አማጽያኑ ወደ ተቆጣጠሩዋቸው ቦታዎች አምረዋል።የወታደራዊ ተሽከርካሪዎቹ
የመጫረሻ መዳረሻ የት እንደሆነ እስካሁን አለመታወቁ በዓለማቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ሳይቀር ግርታን ፈጥሩዋል። ሩሲያ በርካታ ከባድ
ተሽከርካሪዎቹዋን ወደ ስፍራው እያጉዋጉዋዘች ያለችው ለዩክሬን ዓማጽያን ወታደራዊ ድጋፍ ለማቅረብ ነው በማለት ክስ እየቀረበባት
ቢሆንም፤ ሞስኮ ክሱን አስተባብላለች።ዩክሬን በበኩሉዋ ተሽከርካሪዎቹ በዓለማቀፍ ተቆጣጣሪ ቡድን ምርመራ እንዲደረግባቸው
እየጠየቀች ነው። በዩክሬን የተከሰተውን ውጥረት ተከትሎ ራሽያ ከአሜሪካና ከአውሮፓ ጋር ከፍ ወዳለ ፍጥጫ ውስጥ ምግብቱዋ
ይታወቃል።ከቀናት በፊትየቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር ከአሜሪካና ከአውሮፓ ሀገራት ወደ ሩሲያ ይገቡ በነበሩ የእርሻና የእንሣሳት
ምርት ውጤቶች ላይ እቀባ እንዲደረግ ወሳኔ ማሳለፉ፤ በተለይ በብራሰልስና- በሩሲያ መካከል የተፈጠውን ፍጥጫ ወደ ግልጽ
ኢኮኖሚያዊ ጦርነት እንዳሸጋገረው ተንታኞች እየገለጹ ነው።