ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት ሶስት ቀናት ጋብ ብሎ የነበረው የእስራኤልና የፍልስጤማውያን ግጭት እንደገና ማገርሸቱን እስራኤል አስታውቃለች።
በግብጽ አደራዳሪነት ሲካሄድ የነበረው የሰላም ድርድር ሃማስ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፉን ተከትሎ እስራኤል የአየር ድብደባ ጀምራለች።
ሃማስ የሰላም ድርድሩ እስራኤል በጋዛ ላይ ያደረገቸውን ከበባ ማስቆም አለበት የሚል አቋም ይዟል፡፤ እስረኤል በግብጽ በመካሄድ ላይ ያለውን የሰላም ድርድር አልሳተፍም
በማለት ልኡካኖቿን አስወጥታለች።
ከ1900 በላይ ህይወት የቀጠፈው ጦርነት እንደገና የሚራዘም ከሆነ፣ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ዲፐሎማቶች አስጠንቅቀዋል።