መድረክ የኢህአዴግን የኃይል እርምጃ አወገዘ

ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕገ-መንግስታዊ ሰብአዊና ዴሞክራስያዊ መብቱ ተከብረው ሥራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግ እያካሄደባለውቁርጠኝነትየተሞላበትሕዝባዊዴሞክራሲያዊትግልናየኢህአዴግአምባገነናዊአገዛዝ የሕዝባችንንየመብትጥያቄዎችአፍኖለመግዛትእያካሄደ

ባለው የማይሳካለት ጥረት መካከል ያለው ቅራኔ እየሰፋና
እየተባባሰበ መምጣቱ ለረጅም ጊዜ በአምባገነናዊ አገዛዝ ለመቀጠል የነበረው ምኞትስጋት ውስጥ እንደወደቀ የተረዳውኢህአዴግለመብታቸውጠንክረውየሚንቀሳቀሱትንሰላማዊ

ታጋዮችበሽብርተኝነትእየወነጀለበማሰርና በማሰቃየትላይይገኛልሲልመድረክአስታወቀ።

የኢትዮጵያፌዴራላዊዴሞክራሲያዊአንድነትመድረክሰሞኑን ‘ሰላማዊተቃዋሚዎችንበሽብርተኝነትበመወንጀል ሕዝባዊዴሞክራሲያዊትግልንመግታትናሕገ-መንግስታዊ

መብቶችንረግጦመግዛትአይቻልም!!!’ በሚልርዕስ ባወጣውመግለጫኢህአዴግበዚሁአካሄዱበየጊዜውበሚወስዳቸውየተሳሳቱእርምጃዎችዜጎችበሕገ-መንግስቱ
የተረጋገጡትንመብቶችበአግባቡእንዳይጠቀሙግራየሚያጋባውዥንብርእየፈጠረይገኛል።በዚህየኢህአዴግተግባር የኢትዮጵያፌዴራላዊዴሞክራሲያዊአንድነትመድረክ

የአመራርአባላትናደጋፊዎችእንደዚሁምየሌሎችተቃዋሚ ፓርቲዎችየአመራርአባላትናአባላትሰለባእየሆኑይገኛሉብሏል።
የመድረክአባልየሆነውየአረናትግራይለዴሞክራሲናሉአላዊነትፓርቲየሥራአስፈፃሚኮሚቴ አባልናየመድረክጠ/ጉባዔአባልየሆኑትናየገዥውንፓርቲኢ-ሰብአዊናፀረ-ዴሞክራሲያዊ

አገዛዝንናአሰራሮችን ሕገ-መንግስታዊኀሳብንበነፃነትየመግለጽመብትተጠቅመውበተለያዩጽሑፎችበቆራጥነትሲያጋልጡየቆዩትአቶ አብርሃደስታከሚኖሩበትናከሚሰሩበትመቀሌ ከተማ ተወስደው

አዲስአበባበማምጣትከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮእንዲታሰሩመደረጋቸውን ያስታወሰው መድረክ፣  ቤተሰቦቻቸውናየትግልጓዶቻቸውምእንዲያገኙዋቸው አለመፈቀዱን ገልጿል።

በትግራይክልል ደቡባዊዞንየአረናአስተባባሪየሆኑትአቶአደሃኖምንጉሴ፣በምዕራብዞንከሁመራአቶገብረዋሂድአስመሮምና አቶተክላይዘውዱምበእስርላይእንደሚገኙ የጠቀሰው መድረክ፣  በእንደርታ

ወረዳ 8፣በውቅሮወረዳ 3፣በአጽቢ ወንበርታወረዳ 1 አባሎቻቸውበሽብርተኝነትተወንጅለውመታሰራቸውን ገልጿል።

በሃውዜንናበሌሎችወረዳዎችምበብዙመቶዎችየሚቆጠርህዝብየአረናደጋፊዎችናችሁተብሎየማስፈራሪያዛቻ እየደረሰባቸውናእየታሰሩመሆኑንም ግንባሩ አስታውሷል።

በኦሮሚያክልልደግሞ የመድረክአባልበሆነውበኦፌኮአባላትናደጋፊዎችላይ
አፈሳናእሥራትምእጅግተባብሶየቀጠለ ሲሆን    በወለጋቂለምአቶዱላማቴዎስ፣  አቶገመቹሻንቆ ፣አቶራጋአማናአቶሀብታሙብርሃኑየተባሉየዞኑየኦፌኮ አመራርአባላትንጨምሮ 158

አባላትናደጋፊዎችበአንፊሎናበደምቢዶሎከተሞችበእሥርላይእንደሚገኙ ጠቅሷል።

ፍ/ቤት የዋስመብታቸውንቢጠብቅላቸውምፖሊስየፍርድቤቱንትዕዛዝሥራላይለማዋልፈቃደኛሆኖባለመገኘቱእስከ አሁንበእሥርላይእንደሚገኙ የገለጸው ግንባሩ፣

በምዕራብወለጋዞንየዞኑየኦፌኮአመራርአባልየሆኑትአቶሀምባፉፋንጭምሮከ100 በላይአባላትና ደጋፊዎችላለፉትሦስትወራትበግምቢታስረውየሚገኙሲሆን፤እስካሁንበሕግ

አግባብፍርድቤትአልቀረቡም።በምዕራብሸዋዞንበአምቦናአካባቢዋየኦፌኮአመራርአባል

የሆኑትአቶቀናአጩጬንጨምሮከ150 በላይ ሴቶችናአዛውንቶችየሚገኙባቸው  አባላትናደጋፊዎችበአምቦወሕኒቤትታስረውይገኛሉ። መድረክ አያይዞም  በኢሉ

አባቦራዞንሁሩሙወረዳናአካባቢዋከ180 በላይየኦፌኮአባላትናደጋፊዎችታሥረውእንደሚገኙና ፍርድ ቤት አለመቀርባቸውን፣    በአዳማዞንየኦፌኮተወካይአቶ ቱሉ

ባቢሳንጨምሮከ50 በላይአባላትናደጋፊዎችበአዳማወሕኒቤትመታሰራቸውን ገልጿል።

በምሥራቅወለጋዞንየኦፌኮአመራርአባልየሆኑአቶአፍሪካከበደንጨምሮከ80 በላይአባላትናደጋፊዎች አዲስአበባበሚገኘውማዕከላዊምርመራሲታሰሩ፣  ከአምቦዩንቨርስቲ

31፣ከድሬደዋዩኒቨርስቲ 21፣  ከወለጋ ዩኒቨርስቲ 32 ተማሪዎችታሥረውእንደሚገኙም ገልጿል።

ከአዲስአበባናዙሪያዋከተሞችጉዳይጋርበተያያዘበሰላማዊመንገድጥያቄሲያቀርቡየነበሩበርካታ ዜጎችንየገደሉአካላትምእስካአሁንለፍርድአለመቅረባቸውን መድረክ ገልጿል።

በክልሉየሚታዩልዩልዩየህዝብችግሮችንየዘገቡበክልሉመንግስትመገናኛብዙሀንሠራተኛየነበሩ 19 ጋዜጠኞችምከሕጋዊየመንግስትሠራተኞችአስተዳደርሥርዓትና

ደንብውጭበሆነሁኔታከሥራቸውመባረራቸውን ግንባሩ ገልጿል።

በአሁኑወቅትበኦሮሚያክልልከላይበተጠቀሱትአካባቢዎችወታደራዊአስተዳደርሰፍኖሕዝቡ በድብዳባ፣በወከባናበእሥራትእየተሰቃየእንደሚገኝ፣  በተለያዩ

አካባቢዎችበሙስሊምወገኖችላይየእምነት ነፃነታቸውንበመጣስየሚፈፀመውእሥራትናወከባምበሰፊውእንደቀጠለመሆኑን ጠቅሷል።

የአንድነትለፍትህናለዴሞክራሲፓርቲአመራርአባላትየሆኑትአቶሀብታሙአያሌውናአቶዳንኤል ሺበሺእንደዚሁምየሰማያዊፓርቲአመራርአባልየሆኑትአቶየሺዋስአሰፋ

በተመሳሳይወንጀልበአሁኑወቅት ታሥረውእንደሚገኙ ያስታወሰው መድረክ፣  በሚቀጥለውዓመትይካሄዳልተብሎለሚጠበቀውሀገርአቀፍምርጫየፖለቲካምህዳሩንና

የምርጫሜዳውንማመቻቸት ስለሚቻልበትናየሀገራችንንውስብስብፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና፣ማኅበራዊችግሮችንመፍታትስለሚቻልበትሁኔታ ገንቢውይይትናድርድር

ከተቃዋሚፓርቲዎችጋርማካሄድንአሻፈረኝብሎየሚገኘውኢህአዴግበአምባገነናዊአገዛዙ ለመቀጠልእንዲችልተቃዋሚፓርቲዎችንናእንቅስቃሴያቸውንበኃይል

ለማዳከምያስችለኛልብሎየገመታቸውንየኃይል
እርምጃዎችሁሉበአሁኑወቅትማስፋፋቱየጠቅላይነትናብቸኛገዥፓርቲነትምኞቱነፀብራቆችናቸው ብሎአል።
ኢህአዴግበእነዚህአምባገናዊየኃይልእርምጃዎችየዜጎችንበሰላማዊመንገድየመቃወምሕገ-መንግሥታዊ መብቶችለመግፈፍየሚፈጽማቸውንየማሰርናየማሰቃየትእርምጃዎች

በአስቸኳይእንዲያቆምናከዚህበላይየተገለፁትን ሰላማዊታጋዮችበአስቸኳይእንዲፈታየኢትዮጵያፌዴራላዊዴሞክራሲያዊአንድነትመድረክጠይቋል።