ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ኤጀንሲ እንደገለጸው ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በብዙ አገሮች የኤደስ ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነ ሲሆን ፣
ስርጭቱንም ከ14 አመታት በሁዋላ ማቆም እንደሚቻል ገልጿል።
አሁንም በርካታ ዜጎች መድሃኒት አጥተው በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ገልጿል። በዚህ አመት በአለም ደረጃ 2 ሚሊዮን 300 ሺ ሰዎች ብቻ በኤች አይ ቪ ቫይረስ ተይዘዋል።
በአጠቃላይ በአለም ላይ 35 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ በቫይረሱ ተይዟል።