ሰኔ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባልታሰበ ቅጽበት የተለያዩ የሰሜን ኢራቅ ከተሞችን እየተቆጣጠሩ የመጡት የሱኒ ኢስላሚክ ታጣቂዎች ፣ ዋና ከተማዋን ባግዳድን ለመያዝ በቅርብ እርቀት እየተፋለሙ ሲሆን፣ አሜሪካ የኢምባሲ ሰራተኞቹዋን ለማሸሽ ሽፋን የሚሰጡ ከ250 በላይ የጦር ሰራዊቷን መላኩዋ ታውቋል።
የእግረኛ ሰራዊት ለመላክ እንደማትሻ ያስታወቀችው አሜሪካ፣ በኢራቅ ላይ ስለምትወስደው እርምጃ ውሳኔ ላይ አልደረሰችም።
እስላሚክ ታጣቂዎቹ ባግዳድን ከተቆጣጠሩ ከሺያ ታጣቂዎች ጋር ደም አፋሳሽ ጦርነት ሊያደርጉ ይችላሉ።
የፖለቲካ ተንታኞች ኢራቅ ለ3 ልትከፈል እንደምትችል እየተናገሩ ሲሆን፣ የአገሪቱ መንግስት ግን ታጣቂዎችን እንደሚያሸንፋቸው እየዛተ ነው።