ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የግንቦት 20 በዓል በተከበረበት ወቅት ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት
ንግግር ኢትዮጵያ በምግብ ሰብል እህል ምርት ራሱዋን መቻሉዋን ተናግረዋል።
ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው የዋና ዋና ምግብ ሰብሎች ምርት በ2002 ከነበረበት 202 ሚሊየን ኩንታል፣በ2005 ዓ.ምወደ 251 ሚሊየንኩንታልቢያድግምከሚጠበቀውአንጻርእድገቱዝቅተኛመሆኑንይጠቅሳል ፡፡ይህምጠ/ሚኒስትሩ በምግብ ራሳችንችለናልከሚልገለጻቸውጋርየሚጋጭ ሲሆን ኢህአዴግ በባህርዳር ከተማ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የሰብል ልማት በእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከተቀመጠው በታች መሆኑን ከገለጸበት ሪፖርት ጋር ሲተያይ የአቶ ሃይለማርያምን ንግግር ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል።
ኢህአዴግ በጉባኤው ሪፖርት ላይ የሰብልን ምርት በተመለከተ ” ባሰብነውፍጥነትተጉዘንያስቀመጥነውግብላይያልደረስነውለሠራዊትግንባታየተመቸሁኔታከመፍጠርአልፈንሠራዊቱንበሁሉምቦታበተሟላመልኩመገንባትየሚያስችለንቁመናላይ” ባለመሆናችን ነው ብሎአል።
“በየደረጃውያለውአመራርቁርጠኝነትመጓደል፣የማስፋትዕቅዳችንንበጥብቅዲሲፒሊንመፈፀምናማስፈፀምአለመቻል፣የሙያተኛውንና
የአርሶአደሩንአቅምበሚፈለገውመልኩገንብተንአለመንቀሳቀስ” ዋና ዋና ችግሮች ተብለው ቀርበዋል።
ዘጋቢያችን ያነጋገረቻቸው የአዲስአበባነዋሪእንደተናገሩትበመላአገሪቱቀርቶበአዲስአበባከተማ ውስጥበቀንሶስትጊዜዳቦእንኩዋንማግኘትያልቻሉበርካታየተራቡዜጎችመኖራቸውየአደባባይሚስጢርመሆኑን በማስታወስየጠ/ሚኒስትሩንግግርፌዝነውብለውታል፡፡
በአሁኑወቅትየጤፍዋጋበኩንታልሁለትሺብርመሆኑን ያስታወሱትእኚህአስተያየትሰጪደሃጥራጥሬእንኩዋንበርካሽዋጋአግኝቶመመገብያልቻለውየእርሻምርቶች ዋጋከአቅምበላይበመሆኑነውብለዋል፡፡ በቂምርትቢኖርኖሮየእህልዋጋምየመቀነስናየዋጋግሽበቱምበተጨባጭየመረጋጋትአዝማሚያይኖረውነበርሲሉአክለዋል፡፡
እ.ኤ.አበ2013 ለሁለተኛውግማሽዓመት (ከጁላይእስከዲሴምበር) ከአደጋክስተትጋርበተገናኘየአስቸኩዋይጊዜየእለትዕርዳታድጋፍያስፈልገዋልተብሎበጥናትለተረጋገጠው 2 ነጥብ 7 ሚሊየንሕዝብ 166 ሚሊየን176 ቶንምግብየቀረበሲሆንይህምከፍላጎቱአንጻርሲለካአቅርቦቱ 69 በመቶያህልነው፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ ባወጠው ሪፖርት ደግሞ ከ6 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ።
ከግብርናሚኒስቴርየተገነመረጃእንደሚመለክተው ደግሞበያዝነው 2006 በጀትኣመትብቻ 2 ሚሊየን 158ሺህ 429ኢትዮጵያዊያንስርበሰደደየምግብዋስትናችግርውስጥበመግባታቸውበመረዳትላይመሆናቸውአረጋግጧል።
ኢህአዴግበቀድሞሊቀመንበሩአቶመለስዜናዊአማካነትህዝቡበቀንሶስትጊዜእንዲበላለማድረግየገባውቃልከ23 ዓመትበኃላምተፈጻሚማድረግአለመቻሉሳያንሰውበምግብራሳችንችለናልየሚልአዲስማደናገሪያመምጣቱአስገራሚእንደሆነባቸውአስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል።