ግንቦት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና በተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር መካከል የተጀመረው ጦርነት ከ4 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ለረሃብ ማጋለጡን ተከትሎ በኖርዌይ በተካሄደው የእርዳታ ማሰባሰብ ስራ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ተገኝቷል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ችግሩን ለመቅረፍ ከ1 ቢሊዮን 800 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ እየገለጸ ነው።
በርካታ ገበሬዎች በጦርነት የተነሳ ማረስ እንዳልቻሉ እና የረሃቡም መንስኤ ጦርነቱ መሆኑን ድርጀቱ ገልጿል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን በረሃብ የተነሳ መሞታቸውን ድርጀቱ አስታውቋል።