ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላው የኦሮምያ አካባቢ የተነሳው ተቃውሞ ደም አፋሳሽ በሆነ ሁኔታ እንደቀጠለ ሲሆን ዛሬ በባኮና አካባቢዋ እንዲሁም በቡራዩ ነዋሪዎች ተደብደብው ጉዳት ደርሶባቸዋል። በርካታ ሰዎች መታሰራቸውም ተሰምቷል። እስካሁን ድረስ ከ40 ያላነሱ ሰዎች በተለያዩ የኦሮሞያ አካባቢዎች መገደላቸውን፣ ከ300 በላይ መቁሰላቸውንና ከ1 ሺ500 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መታሰራቸውን ከክልሉ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በባኮ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲያሰሙት በዋሉት ተቃውሞ የሌሎች አካባቢ ተወላጆች ትግሉ የዲሞክራሲ በመሆኑ እንዲቀላቀሉዋቸው ጠይቀዋል
በቡራዩ የተነሳውን ተቃውሞ የፌደራል ፖሊሶች ለመቆጣጠር ሙከራ አድርገዋል። ውጥረቱ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ከ200 በላይ ወጣቶች ታፍሰው ታስረዋል
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፌደራል ፖሊሶች ተቃውሞ ሊያስነሱ ይችላሉ ብለው የጠረጠሩዋቸውን ተማሪዎች ይዘው ማሰራቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ኳስ በስክሪን እየተመለከቱ በነበረበት ወቅት ማንነቱ ባልታወቀ ሰው በተወረወረ ፈንጂ 2 ተማሪዎች መገደላቸውንና ከ150 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸውን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። መንግስት በበኩሉ 70 ተማሪዎች ብቻ እንደቆሰሉ መግለጫ ሰጥቷል። በዩኒቨርስቲው ከፍተኛ ጭንቀት መኖሩን ተማሪዎች ሲናገሩ፣ የቻሉት ከዩኒቨርስቲው እየለቀቁ ወደ ከተማዋ እየተሰደዱ ነው።
አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ተማሪዎች ሲወጡና ሲገቡ የሚፈተሹ በመሆኑ ቦንቡን ተማሪዎች አፈንድተውታል ብሎ ለመናገር አይቻልም። አንዳንድ ተማሪዎች ፍንዳታውን ምናልባትም የብሄር ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ ፖሊሶች ሆን ብለው ሳያፈነዱት አልቀረም ይላሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር በህወሃት ኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች የተወሰደውን እርምጃ ኮንኗል።
የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ የሰብአዊ መብትና የአገሩ ባለቤት የመሆን ጥያቄ ነው ያለው ኦዴግ፣ የኦሮሞ ተወላጆች በፖለቲካ አቋም፣ በእምነትና በሌሎችም ምክንያቶች ሳይለያዩ እንዲሰባሰቡና ትግሉን እንዲያፋፍሙና ለህዝቡ በአንድነት እንዲደርሱ፣ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም የኦሮሞን ህዝብ ግድያና እስር በዝምታ መመልከቱን ትተው ተመሳሳይ ችግር ነገም በእነሱ ላይ ሊደርስ እንደሚችል በመገንዘብ ከኦሮሞ ህዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል።
የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ሌንጮ ባቲ ” ይህ የ90 ሚሊዮን አገር ነው፣ ኢትዮጵያን ሁሉ ያካተተ ምክክር እንደሚያስፈልግ” ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የሚቀጥለውን ወሳኝ ምእራፍ ካላለፈች ወይም በሚቀጥለው ወሳኝ እርምጃ ላይ አንክሳ የምታልፍ ከሆነ በጣም መጥፎ ነው ሲሉ ተናግረዋል የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት በበኩሉ በተለያዩክልሎችየሚገኙናበሰላማዊመንገድተቃውሞአቸውንሊገልጹበወጡየኦሮሞተወላጆችላይየጥይትናዳውንአውርዶግድያመፈጸሙን፤በጎንደርምእንዲሁከመሬትመፈናቀልጋርበተደረገተቃውሞሰልፍንፁሃንኢትዮጵያውያንህይወታቸውበግፍመነጠቃቸውን አስታውሶ ፣ የወያኔስርዓትትናንትአንዱንብሄረሰብናሀይማኖት፤ዛሬሌላውን፤ነገደግሞባለተራውንበየተራሲያጠቃ፤ሁላችንምየአንዱኢትዮጵያዊጥቃትየኔምነውብለንበህብረትእስካልተቃወም ነውናእስካልተነሳንድረስጥቃቱናበደሉእየተባባሰ እንደሚሄድያሳለፍነው 22 አመትየመከራታሪክምስክርነው ብሎአል።
የሽግግር ምክር ቤቱ ” ይህንንስርየሰደደመርዘኛየወያኔየዘርናየሃይማኖትፖለቲካንየምንዋጋው፤ስርዓቱንበማስወገድዘላቂየሆነየዲሞክራሲያዊስርዓትለመገንባትሁላችንምበኢትዮጵያዊነትበጋራስንቆምናስንታገልነው” ብሎአል።
በሌላ ዜና ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በነቀምትና አምቦ መካከል ባሉ አካባቢዎች ሰራተኞቹ እንዳይንቀሳቀሱ መመሪያ አስተልለፎአል። በአምቦ የተካሄደው ተቃውሞ ከፍተኛ እንደነበር ድርጅቱ አመልክቶ፣ ተጨማሪ መልእክት እስከሚተላለፍ ድረስ ሰራተኞች እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።