የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዩክሬን የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ አዲስ መንግስት መመስረቱ ያስቆጣት ሩስያ ክሪሚያ የምትባለውን የዩክሬን ግዛት አውሮፕላን ማረፊያን በማቆጣጠር ተጽእኖ ለመፍጠር እየሞከች ነው።
በክሪሚያ ግዛት 60 በመቶ የሚሆኑት ሩስያውያን ሲሆን፣ ሩሲያ ዜጎቿ ከጥቃት ለመከላከል በማሰብ የወሰደችው እርምጃ መሆኑን ትናገራለች። የምእራባዊያን አገራትና ጊዜያዊው የዩክሬን መንግስት የሩሲያን እርምጃ ግልጽ ወረራ በማለት አውግዘውታል። የሩሲያው መሪ ቭላድሜር ፑቲን የዩክሬንን ግዛት እንደሚያከብሩ ቢገልጹም፣ ወታደሮቻቸው በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ የጦር ልምምድ እያደረጉ ነው።
ከስልጣናቸው የተባረሩት የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ያኑኮቪች በአሁኑ ሰአት ሩሲያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ ህጋዊው የአገሪቱ መሪ እኔ ነኝ ማለታቸውንም የውጭ የመገናኛ ብዙሀን ገልጸዋል።
ክሪሜያ ቀደም ብሎ በሩሲያ ተይዛ የነበረ ሲሆን፣ በፈረንጆች አቆጣጠር በ1954 ፣ ሩሲያ ለዩክሬን አስረክባለች።