ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአፍሪካ በመርከብ ተሳፍረው ወደ አውሮፓ ለመግባት የሞከሩ 1 ሺ 100 የሚጠጉ ስደተኞች በጣሊያን ፖሊሶች እርዳታ አውሮፓ እንዲገቡ ተድርጓል።
ከዚህ በፊት ላምባዱሳ እየተባለ በሚጠራው የጣሊያን ግዛት አካባቢ ከደረሰውን አሰቃቂ አደጋ በሁዋላ የጣሊያን ፖሊሶች ወደ አውሮፓ የሚገቡ አፍሪካውያንን ህይወት እየታደጉ ይገኛል።
ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ ወደ አውሮፓ ከገቡት መካከል 50 ህጻናትና 47 ሴቶች ይገኙበታል። ስደተኞች ወደ አውሮፓ ከገቡ በሁዋላ አብዛኞቹ ህጋዊ ወረቀት አያገኙም።