ታህሳስ ፲( አስር )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ300 ሺ በላይ አባላት ያሉት የደቡብ አፍሪካ የሜታል ሰራተኞች ማህበር ደቡብ አፍሪካ ነጻ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ በስልጣን ላይ ያለውን የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ሲደግፍ ቆይቷል።
ማህበሩ ለማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ድጋፉን እንደማይሰጥም አስታውቋል። የፕሬዚዳንት ዙማ መንግስት ሙስናንና ድህነትን በመዋጋት በኩል በቂ ስራ አልሰራም በሚል እየተተቸ ነው።
የሰራተኛው ማህበር ከታዋቂው ነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ሞት በሁዋላ በገዢው ፓርቲ ላይ ያለውን ተቃውሞ በመግለጽ የመጀመሪያ ሆኗል። ፕሬዚዳንት ዙማ በኔልሰን ማንዴላ የቀብር ስነስርአት ላይ ከህዝባቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞቻው ነበር።