ታህሳስ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ 62 በመቶ የሚሆኑት ከ 20- 49 እድሜ ክልል የሆናቸው ሴቶች ጋብቻ የመሰረቱት እድሚያቸው ከ 18 ዓመት በታች በነበሩበት ወቅት ነው፡፡
አቶ ተስፋየ ተካ የህዝብ ጤና ባለሙያ ባደረጉት ጥናት በላፈው ዓመት ልዩነቶችን ለማወቅ በተካሄደ ጥናት በአማራ ክልል ያለ እድሜ ጋብቻ ከፍተኛውን መጠን እንደያዘ ይኸው ጥናት ይጠቁማል፡፡48 በመቶ በገጠር 28 በመቶ በከተማ ያገቡ ሴቶች ዕድሚያቸው 15 ከመሙላቱ አስቀድመው ነበር፡፡
ከዚህ በፊት ያገቡ ሴቶች ላይ በተደረገ መጠየቅ ከ 60 በመቶ በላይ የሆኑት ሴቶች ከማግባታቸው በፊት ሰለ ጋብቻው ምንም ዓይነት መረጃ አልነበራቸውም፡፡ 72 በመቶ ያህሎች ማግባት ይኑርባቸው ወይንም አይኑርባቸው የራሳቸውን ማረጋገጫ ያልሰጡ ነበሩ፡፡75 በመቶ ያህሉ ከባሎቻቸው ጋር ከጋብቻው በፊት ፈጽመው የማይተዋውቁ ናቸው፡፡
መንግስት የድርሻውን አለመወጣቱ የማስተማር ስራውን በአግባቡ ባለመወጣቱ ከፍተኛ ችግር በጤና እና በማህበራዊ እና ዘርፍ እንዲከሰት በር ከፍቱዋል፡፡ከዚህ በፊት ያገቡ ሴቶች ላይ በተደረገ መጠይቅ 55 በመቶ ያህል ለማግባታቸው ምክንያት የሌሎች ግፊት እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ የዚህም ግፊት ምንጮች አባቶች 91 በመቶ፣ እናቶች 88 በመቶ ፤ በአገር ሺማግሌዎች 22 በመቶ ነው።
በኢትዮጵያ በ2005 በተደረገው የጤና ዳሰሳ መሰረት ዕድሜያቸው በ15 እና በ19 ዓመት መሃል የሆኑት 13 በመቶ የሚሆኑት ሴት ልጆች ያገቡት በ15 ዓመታቸው ነበር፡፡
በተነፃፃሪነትም 32 በመቶ የሚያክሉት ዕድሚያቸው ከ25-34 ያሌት ሴቶች ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ማግባታቸው ተመልክቷል፡፡
ያላቻ ጋብቻ በሴት ልጆች ላይ ከፍተኛ የሆነ የጤና እንዲሁም የማበራዊ ደህንነት ህልውና ላይ ያለው ጉዳት እና አደጋ ከፍተኛ ነው፡፡ በኢትዩጵያ ተጨባጭ ችግሮች በጥናቱ እንደተወሳው 27 በመቶ በከተሞች 19 በመቶ በገጠር ያላገቡ ሴቶች ከትዳራቸው ተፋተዋል ወይንም ተለያይተዋል፡፡
ከአንድ ጊዜ በላይ ጋብቻ የፈፀሙ ደግሞ 56 በመቶ ያህሎች የመጀመሪያ ጋብቻቸው የተጠናቀቀው በጣም ልጅ ሰለነበሩ ወይንም ፍላጎት ስላልነበራቸው እነደነበር ለቀረበላቸው መጠይቅ መልስ ሰጥተዋል፡፡