ጥቅምት ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዘውዲቱ ሆስቲታል መድሀኒቱን ለመቀበል ከሳምንታት በላይ ሲጠባበቁ የነበሩ የስኳር ህመምተኞች በመጨረሻ መድሀኒት የለም መባላቸውን ለኢሳት ገልጸዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሰጠው እርዳታ መቋረጥ ለችግሩ መፈጠር ምክንያት ነው ቢባልም፣ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ የችግሩ ምንጭ መድሀኒቱ አየር ባየር ስለሚሸጥ ነው ብለዋል።
ህመምተኞች እንደሚሉት መድሀኒቱን በግላቸው ገዝተው ለመጠቀም ዋጋው የሚቀመስ አይደለም። ብዙዎቹ መድሀኒቱን ለማግኘት ባለመቻላቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።