ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእየአመቱ የሚከበረው የኢድ-አል አድሃ ( አረፋ) በአል ኢብራሂም ልጁን ለመስዋት ያቀረቡበትን እለት ለመዘከር ነው።
በአዲስ አበባ በተካሄደው የበአል አከባበር ስነስርአት ከዚህ ቀደም ያልታዩ ክስተቶች ታይተዋል። ዘወትር እንደሚደረገው የመጅሊስና አዲስ አበባ መስተዳድር ባለስልጣናት ንግግር አላደረጉም። ድምጻችን ይሰማ ትናንት ባወጣው መግለጫ የመንግስት ባለስልጣናት ወይም የመጅሊስ አመራሮች መልእክቶችን ለማስተላለፍ ንግግር ማድረግ ከጀመሩ ህዝቡ በተቃውሞ እንዲያቋርጣቸው መመሪያ አስተላልፎ ነበር። ይህን ተከትሎ በሚመስል ሁኔታ የአዲስ አበባ መስተዳድር ባለስልጣናት ወይም የመጅሊስ አመራሮች ንግግር ከማድረግ ተቆጥበዋል።
የሚመጣውን ተቃውሞ በመፍራት የመንግስት ባለስልጣናት ንግግር አለማድረጋቸው መንግስት ተቆጣጥሬዋለሁ የሚለው የሙስሊሙ ተቃውሞ አሁንም አሰፍሪ ሀይል ሆኖ መጓዙን እንደሚያመልክት ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።