መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአለማቀፍ የቴሌኮሚኒኬሽን ማህበር ባወጣው መረጃ በአለም ካሉ አገራት ጊኒ ቢሳው፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ቻድ፣ ማእከላዊ አፍሪካና ኒጀር የመጨረሻዎቹን ደረጃዎች ይዘዋል።
በተቀራኒው ደቡብ ኮሪያ፣ ስዊድን፣ አይስላንድ፣ ዴን ማርክ፣ ፊንላንድ ፣ ኖርዌይ፣ ኔዘርላንድስ እንግሊዝና ሆንግ ኮንግ ከ አንድ እሰከ አስር ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎትን ለግል ባለሀብቶች እንዲለቅ ግፊት ቢደረግበትም ፈቃደኛ አልሆነም።