መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ከፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት የወጣውን መግለጫ በመጥቀስ እንደዘገበው፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማራዘም ያስፈለገው ከአገሪቱ የ ደህንነት ሁኔታ ጋር በተያያዘ ነው።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገው ባለፈው ነሐሴ ወር በመሀመድ ሙርሲ ደጋፊዎች ላይ የግብጽ ፖሊስና መከላከያ የሀይል እርምጃ መውሰዳቸውን ተከትሎ ነው።
የፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲን ከስልጣን መወገድ በተቃወሙ ደጋፊዎቻቸው ላይ በተወሰደው እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብጻውያን መገደላቸው ይታወሳል።
በግብጽ ታሪክ በህዝብ ድምጽ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት መሀመድ ሙርሲ ባለፈው ሐምሌ ወር የተነሳባቸውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ሠራዊቱ ጣልቃ በመግባት ከስልጣን እንዳነሳቸው ቢቢሲ አስታውሷል።