ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሞያሌ ከተማ በገሪና በቦረና ጎሳዎች መካከል ከሳምንታት በፊት የተነሳው ግጭት እንደገና አገርሽቶ የአካባቢው ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው። የኬንያ መንግስት የጸጥታ ሀይሎችን ወደ አካባቢው በመላክ ግጭቱን ለመከላከል እየሞከረ መሆኑን ቢናገርም ችግሩ ግን ተባብሶ መቀጠሉን የኬንያ ጋዜጦች አየዘገቡ ነው። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ20 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። በአካባቢው የሚገኙ የንግድ ቤቶች ሲወድሙ ትራንስፖርትም ቆሟል። የኬንያ ሞያሌ ነዋሪዎችም ከተማዋን ለቀው እየወጡ ነው።
በገርባና በቦረናዎች መካከል ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ ግጭት ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል። የኢትዮጵያ እና የኬንያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በአካባቢው ቢሰፍሩም ግጭቶች ለማስቆም አለመቻላቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።
ቦረናዎች ከጉጂና የሶማሌ ጎሳ ከሆኑት ገሪዎቸም ጋር እንዲሁ በየጊዜው ጦርነት ያደርጋሉ።