ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-አራጣ በማደበር ተከስሰው 25 ዓመት የተፈረደባቸው አየለ ደበላ በቅጽል ስማቸው አይ ኤም ኤፍ የቀብር ስነስርአት በቅድስት ስላሴ ካቴደራል በከፍተኛ ስነስርዓት ተፈጽሙዋል፡፡
አቶ አየለ የባንክን ሥራ ተክተው በመሥራት፣ አራጣ በማበደር፣ ግብር ባለመክፈልና በሌሎችም ክሶች ጥፋተኛ ተብለው በከፍተኛው ፍርድ ቤት በ22 ዓመታት እስርና በባንክ ያላቸው 12 ሚሊዮን ብር እንዲወረስ ከተወሰነ በሁዋላ፣ አቃቢ ህግ ይግባኝ በመጠየቁ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በ25 ዓመታት እንዲታሰሩና እንዲወረስ የተወሰነው ገንዘብ እንዲፀና ውሳኔ አስተላልፎ ነበር።
አቶ አየለ ደበላ ከፍተኛ ተደራራቢ ሕመም እንዳለባቸው ለፍርድ ቤት በቅጣት ማቅለያነት አቅርበው የነበረ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።