ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-ኢሳት ዜናውን ይፋ ካደረገው በሁዋላ የሟቹ ጓደኛ የሆነ አንድ ግለሰብ መረጃውን ለሟቹ ባለቤት በሚስጢር ማስተላለፉንና ባለቤቱ እና ልጆቹ በጋራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል በመሄድ አስከሬኑን መለየታቸው ታውቋል። ባለቤቱ አስከሬኑን ለመለየት የቻለችው በሰውነቱ ላይ ባለው ልዩ ምልክት ሲሆን፣ ጉዳዩን ለማጣራትም ወደ ቤተመንግስት በመሄድ የባለቤቷን አድራሻ መጠየቋ ታውቋል። ከቤተ-መንግስት የተሰጣት መልስ ሟቹ ለልዩ ተልእኮ ወደ ታንዛኒያ ተልእኳል የሚል መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
ግለሰቡ የደቡብ ተወላጅ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ በቤተመንግስት ውስጥ ስለነበረው የስራ ድርሻ ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። የግድያውን ምክንያት ለማጣራት እየሞከርን ሲሆን መረጃው እንደደረሰን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን።
ማቹ ከአቶ ሀይለማርያም ጽህፈት ቤት ከ150 እስከ 200 ሜትር በሚደርስ እርቀት በሁለት የስለላ ከሜራዎች መካከል ተጥሎ መገኘቱን መዘገባችን ይታወቃል።