ግንቦት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአገራቸው ጉዳይ ላይ ላለፉት 3 አመታት ለኢሳት ስልክ በመደወል አስተያየታቸውን ሲሰጡ የቆዩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቢኖሩም የ12 አመቱ የስድስተኛ ክፍሉ የወንድይራድ ተማሪ ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልእክት በማስተላለፍ በኢሳት ታሪክ የመጀመሪያው ታዳጊ አስተየየት ሰጪ ሆኖ ተመዝግቧል።
ታዳጊው ግንቦት25 ፣ 2005 ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተገኝቶ የተመለከተውን ተናግሯል።
በጣፋጭ ለዛና በአስደናቂ የቋንቋ አጠቃቀም መልእክቱን ያስተላለፈው ታዳጊ፣ ” ስለአገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ምሁሩ ገበሬው ፣ ወዛደሩ ፣ ጋዜጠኛው ፣ ተፈናቃዩ፣ ስደተኛው ሁሉ በሚችለው ቋንቋ ይጽፋል፣ ይናገራል፣ በህጻን አእምሮየ ይህን ሁሉ ስሰማ እውነትም ሀገሬ አንድ ነገር እንደሆነች ተሰምቶኛል።” ብሎአል።
ስለአገሬ በቂ እውቀት ያገኘሁ በመሆኔም ከእንግዲህ እየተማርኩ እታገላለሁ፣ እየታገልኩ እማራለሁ፣ ስለአገራችን ምንም እውቀት የሌላቸውን የእድሜ እኩዮቼን የተረዳሁትን ለማስረዳት ቃል እገባለሁ” ሲል አክሎአል ። ከትምህርት ቤት እንደወጣ ኢሳትን ለማየት እንደሚጓጓም ገልጿል