ሚያዚያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ደቡብ ሱዳንና ሰሜን ሱዳንን እያወዛገበ ባለው በነዳጅ ዘይት በበለጸገችው የአቤይ ግዛት በማጆክና በሚሴሪያ ጎሳዎች መካከል በተደረገ ጦርነት 20 ሰዎች ሲሞቱ፣ በአካባቢው በሰላም አስከባሪነት የተሰማራ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ተገድሎ ሌሎች ሁለት ደግሞ ቆስለዋል።
ማጆክ የተባለው ጎሳ ደቡብ ሱዳንን የሚደግፍ ሲሆን ሚሴሪያ ደግሞ ሰሜን ሱዳንን ይደግፋል።
በግጭቱ የተገደለው ኢትዮጵያዊ ወታደር ስም አልተገለጸም፣ የኢትዮጵያ መንግስትም የሟቹን ስም ይፋ አላደረገም።
ከ3ሺ በላይ የኢትዮጵያ ሰራዊት በሱዳን ግዛት ውስጥ በሰላም አስከባሪነት ተሰማርቶ ይገኛል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ሁለቱ መንግስታት ወደ ግጭት ከማምራት እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።