ጥር ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን ዋካ ውስጥ በአካባቢው ባለስልጣናትና በህዝቡመካከል የተፈጠረው ውዝግብ እየሰፋ ወደ አጎራባች አካባቢዎች መዛመቱንከስፍራው ለኢሳት የደረሰው ዜና አመለከተ። በዋካ ከተማ ሲካሄድ የነበረውእስራትና ፍተሻ በሳምንቱ መጀመሪያ በጦጫ ከተማ ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ከክልልበመጡ ባለስልጣናት እሁድ እለት ለስብሰባ የተጠሩ የዋካ ከተማ ነዋሪዎችበስብሰባው ለመገኘት ባለመፍቀዳቸው ስብሰባው ተሰርዟል፤ በዐጎራባች በጦጫወረዳ የተነሳው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለበርካታ ሰዎች መታሰር ምክንያትሆኗል፤የሃገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ ሀያ ስድስት ሰዎች መታሰራቸውንከስፍራው የመጣው ዜና ያስረዳል። በበርካታ ሰዎች ቤት ውስጥ በተደረገ ፍተሻኮምፒውተሮች የተወሰዱ ሲሆን፤በኮምፒውተሩ ውስጥ የዋካን ሕዝባዊእንቅንቅስቃሴ በተመለከተ በቪዲዮ የተቀነባበረ ዘገባ የተገኘባቸው ግለሰብ ወደእስር ቤት ተወስነዋል፤በኮምፒውተሮቹ ላይ በተደረገው ምርምራ ፋይሎችንከውስጥ ለማግኘት ለፖሊሶቹ አስቸጋር ሆኖ በመገኘቱ የአካባቢውባለስልጣናትን ለመገምገምና ውጥረቱን ለማርገብ የተላኩት የደቡብ ክልልከፍተኛ ባለስልጣናት አቶ አለማየሁ አሰፋ በኮምፒውተሮቹ ብርበራ ተሳታፊእንደነበሩ ተመልክቷል፤ኮምፒውተሩን አላስበረብርም ያሉ
ኮምፒውተራቸውን አስረክበው ወደ እስር ቤት መላካቸውምታውቆአል፤እስረኞቹን ህዝቡ በነቂስ እየወጣ እንደሚጎበኝም የመጣው ዜናያብራራል።